የኬጂ ት/ት ክፍል መልዕክት

እነኳን ለ2010 ዓ.ም የት/ት ዘመን በሰላም አደረሰን /አደረሳችሁ/ እያልኩ

ት/ቤታች ለ2010 ዓ.ም ከቀድሞ በበለጠ ለመስራት የበኩሉን ጥራት እያደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በዋነኝነት በ3 ነገሮች ላይ ትኩረት በመድረግ የተነሳ ሲሆን እነርሱም፡-

  1. ጥራት ያለው ት/ት መስጠት
  2. መልካም ስነ-ምግባር
  3. ሙያዊ ክህሎት ናቸው፡፡  በመሆኑም ለነገ ትልቅ ደረጃ መድረስ የዛሬው ስራችን መሠረት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ ቋንቋዎች በመታገዝ በንጹህ እና ማረኪ ግቢ ለለውጥ በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡

ለዚህም ስኬት እንድንደርሰ  ከጎናችን ሆናችሁ ገንቢና አበረታች አስተያየታችሁን ለለገሳችሁን የመንግስት ባለድርሻ አካላት፤ መ/ራን እና ወላጆች  እንዲሁም ማህበረሰቡን  ከልብ እናመስግናለን፡፡

ለቀጣዩ የት/ት ጊዜያትም ከጎናችን እንደማትለዩን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ለመልካም ስራና ለውጥ እጅ ለእጅ እንያያዝ እላለሁ፡፡

በመጨረሻም ለተማሪዎች እና ለተማሪ ወላጆች ሁለተኛ ሙከራ /ቴስት/ ስለደረሰ ከወዲሁ እንዲያጠኑ መልክታችን ነው፡፡

 

መልካም የት/ት ዘመን ይሁንልን!

    አመሰግናለሁ!

  ወ/ሪት አለምፀሐይ ለሜቻ

Contact KG director

alemtsehay

Ms. Alemtshay Lememcha

KG Principal

Telephone: +251-221-120620

P.O.Box: 2237

alemtsehay-lemecha@makkobillischool.com