Second cycle principal message

ለመኮ ቢሊ ት/ቤት ተማሪዎች፤መምህራንና ወላጆች እንኳን ለ2009 የት/ት ዘመን አደረሳችሁ እያልኩ የ2009 ት/ት ከጀመርን እነሆ 2ኛ ወራችንን ጨርሰናል፡፡ በእነዚህም 2 ወራት ውስጥ የመማር ማሰተማሩ ሥራ በተሳካ ሁኔታና በእቅዳችን መሠረት ተከናውነዋል፡፡

     የ1ኛ ሴሚሰተር የመጀመሪያ ፈተና /ቴስት/ለተማሪዎቻችን የሰጠን ሲሆን በህዳር 12 እና 13/09 ዓ.ም ደግሞ 2ኛ ቴስት ለ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች /ከኬጂ-6ኛ/ክፍል ይሰጣል፡፡

     በመሆኑም ተማሪዎች እንዲትዘጋጁ ወላጆች ተማሪዎቻችንን እንድታበረታቱና ጥሩ ውጤት እንዲያሰመዘግቡ እንዲታደርጉ መምህራንም የልፋታችሁ  ፍሬ ያማረ እንዲሆን ተማሪዎቻችሁን በበለጠ እንደታበቁ አሳሰበለሁ፡፡

  አብዲ ዮናስ የ1ኛ ደረጃ ር/መምህር

የኬጂ ት/ት ክፍል መልዕክት

እነኳን ለ2010 ዓ.ም የት/ት ዘመን በሰላም አደረሰን /አደረሳችሁ/ እያልኩ

ት/ቤታች ለ2010 ዓ.ም ከቀድሞ በበለጠ ለመስራት የበኩሉን ጥራት እያደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በዋነኝነት በ3 ነገሮች ላይ ትኩረት በመድረግ የተነሳ ሲሆን እነርሱም፡-

 1. ጥራት ያለው ት/ት መስጠት
 2. መልካም ስነ-ምግባር
 3. ሙያዊ ክህሎት ናቸው፡፡  በመሆኑም ለነገ ትልቅ ደረጃ መድረስ የዛሬው ስራችን መሠረት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ ቋንቋዎች በመታገዝ በንጹህ እና ማረኪ ግቢ ለለውጥ በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡

ለዚህም ስኬት እንድንደርሰ  ከጎናችን ሆናችሁ ገንቢና አበረታች አስተያየታችሁን ለለገሳችሁን የመንግስት ባለድርሻ አካላት፤ መ/ራን እና ወላጆች  እንዲሁም ማህበረሰቡን  ከልብ እናመስግናለን፡፡

ለቀጣዩ የት/ት ጊዜያትም ከጎናችን እንደማትለዩን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ለመልካም ስራና ለውጥ እጅ ለእጅ እንያያዝ እላለሁ፡፡

በመጨረሻም ለተማሪዎች እና ለተማሪ ወላጆች ሁለተኛ ሙከራ /ቴስት/ ስለደረሰ ከወዲሁ እንዲያጠኑ መልክታችን ነው፡፡

 

መልካም የት/ት ዘመን ይሁንልን!

    አመሰግናለሁ!

  ወ/ሪት አለምፀሐይ ለሜቻ

ለመኮ ቢሊ ት/ቤት ተማሪዎች የተማሪ ወላጆችና መምህራን

ት/ቤታችን ፡ የተማሪ መረጃ አያያዝ፣ የመማር ማስተማሩን ስራ ሂደት፣ የወላጅ መረጃ ማግኛና ክትትልን ዘመናዊና ቀላል ለማድረግ ላለፉት ዓመታት  ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ይህን አገልግሎት ይበልጥ የማዘመንና ለአጠቃቀም ምቹ ለማድረግ ት/ቤቱ የስልክና የድረ ገጽ  ሲስተሙን  በአዲስ መልክ አሰርቶ ለአገልግሎት እንዲበቁ ተደርጓል፡፡

ወላጆች ወደ ት/ቤታችን የሚመጡት ለምዝገባ፣በክፍያና በሚጠሩበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ተነሳሽነት ጥቆማ፣ አስተያየት ለመስጠትም ሆነ ስለ ልጆቻቸው በግንባር ተገኝተው ለመወያየት  ት/ቤት በራሳቸው ሰዓት መምጣት እንዳለባቸው እናሳስባለንለ፡፡ ሆኖም ግን የተለያዩ መረጃ ማግኘት የሚችሉበትን አስተያየትና ጥቆማ መስጠት የሚያስችላቸውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መፍጠርና ተጠቃሚ በመሆን መኮ ቢሊ ቀዳሚ የት/ተቋም ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡ የስልክ መረጃ ማዕከላችንን (Robo call attendant) በመጠቀም በ0221-12-06-21 ከየትኛውም ስፍራ በማንኛውም ሰዓት በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በዚህ የስልክ መረጃ ያለ ምንም ውጣ ዉረድ የት/ቤቱን ጠቃሚ የስልክ ቁጥሮች የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች ወቅታዊ  ዜናዎችን  ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህ የስልክ መረጃ ማዕከል ከዚህም ባለፈ የልጅዎን ሳምንታዊ የትምህርት ሪፖርት እና ፈተና ውጤት፣  አመታዊ ካላንድር፣ ወርሃዊ የትምህርት ቤት ክፍያን እና ለአዲስ ተማሪዎች ክፍት ቦታ መኖሩን ለማረጋገጥ መረጃ  ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህን ለማግኘት ግን ወላጆች የልጆቻቸውን የመታወቂያ ቁጥር(አይዲ ቁጥር) እና የሚስጢር ቁጥር (password) ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን የመታወቂያ ቁጥር (አይዲ ቁጥር) ከመታወቂያ ካርዱ ፊትለፊት ገጽ  ላይ እና የሚስጢር ቁጥሩን (password) ደግሞ ከመታወቂ ደብተራቸው የጀርባ ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የስልክ መረጃ ማዕከሉ ለአጠቃቀም ቀላልና የራሱ አጠቃቀም መመሪያ ስላለው አሁኑኑ በ0221-12-06-21 ይደውሉ፡፡      

የት/ቤታችን www.makkobillischool.com ዌብሳይት አጠቃቀም በተመለከተ፡፡

መኮ ቢሊ ት/ቤት  www.makkobillischool.com  በሚል ስም ድረ ገጽ (ዌብ ሳይት) አለው፡፡ ይህ ዌብ ሳይት ት/ቤታችን በፊት ከነበረው ዌብሳይት በጣም ተሸሽሎ የተዘጋጀና ለአጠቃቀም ቀላልና ብዙ ፋይዳዎችን ለት/ቤቱ አስተዳደር ለመምህራን፤ ለተማሪዎች እንድሁም ለተማሪ ወላጆች ሊሰጥ የሚችል የከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሲስተም ውጤት ነው፡፡ ዌብሳይቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች በከፊሉ፡-

 1. የተማሪ ውጤትና ካርድ መስራት፡- ዌብሳይታችን የተሰጠውን የተማሪ ውጤት በየክፍላቸው በማደራጀት ራሱ አቬሬጅና ደረጃ ያወጣል፣ ራሱ የተማሪ ሪፖርት ካርድ ይሠራል፡፡ ወላጆች ወይም ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማወቅ ወይም የሴምስተር እንድሁም የዓመት ሪፖርት ካርድ ለማየት፤ ፕሪንት ለማድረግ በቀላሉ ብለው ወደ ዌብሳይቱ በመግባት Student Mark Sheet የሚለውን በመምረጥ የተማሩበትን የት/ዘመን እንድሁም በመታወቂያ ደብተራቸው ላይ የተገለጸውን ባለ አራት ድጂት መታወቂያ ቁጥር በማስገባት በቀላሉ የትም ሆነው ማየት ይችላሉ፡፡ ከፈለጉም ኮምፒውተራቸው ላይ ዳዉንሎድ ማድረግ ወይም ፕሪንት ማድረግ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ይህ ሠነድ ለማስታወሻነት እንጂ ለሶስተኛ ወገን እንደ ኦፊሻል ማስረጃነት ለመጠቀም ለት/ቤቱ ቀርቦ በትምህርት ቤቱ ሃላፊዎች ፊርማና በት/ቤቱ ማህተም መደገፍ አለበት፡፡ ከ2007 ጀምሮ ወደፊት ወላጅ ወይም ተማሪ የትኛውም ዓመት ላይ ሆኖ መረጃውን ማግኘት ይችላል፡፡
 2. Online Booking and Registration :- ወላጆች ለልጆቻቸው ቦታ ለመያዝ ወይም ለማስመዝገብ የግድ ወደ ት/ቤቱ መምጣት የለባቸውም፡፡   ይህን ሥራ በሁለት ዙር እቤታቸው ወይም የሥራ ቦታቸው ሆነው ማከናወን ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው ለተማሪው ቦታ ለመያዝ ማመልከት ይሆናል፡፡ ይሄውም ብለው በመግባት በግራ ረድፍ ላይ የሚታየውን Registration መጫን፡፡ ከዚያም ቀጥሎ በሚመጣው ሠንጠረዥ ውስጥ የተማሪውን መረጃ በመሙላት ወላጅ ለልጁ የምዝገባ ቦታ እንዲያዝለት ለት/ቤቱ ያመለክታል ማለት ነው፡፡ ት/ቤቱም ማመልከቻው እንደደረሰው በ24 ሰዓት ውስጥ ለተማሪው ቦታ መኖሩና አለመኖሩ በስልክ ወይም በኢሜል ለወላጅ ይገልጽለታል፡፡ ለተማሪው ቦታ መገኘቱንና መያዙን ከት/ቤቱ በሚገለጽበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ወላጅ Download ከሚለው የዌብሳይቱ ገጽ ውስጥ Registration Form ፕሪንት አድርጎ በመሙላትና በመፈረም ከአስፈላጊ ክፍያ ጋር ወደ ት/ቤቱ በመላክ ምዝገባውን ማከናወን ይችላል፡፡
 3. የትምህርት ቤቱ ጠቃሚ መረጃዎች፡- ዌብሳይቱ የት/ቤቱን ጠቃሚ የስልክ ቁጥሮች ፤ የሥራ ሃላፊዎች ስምና የስልክ ቁጥሮች ይሰጣል፡፡ የት/ቤቱን የበላይ ሃላፊዎች፤ ዳይሬክተሮች፤ ድፓርትመንት ሃላፊዎች፤ ስም ጠሪ መምህራን፤ የፋይናንስ ሃላፊዎች፤ የጥበቃ ሠራተኞች፤ የወላጅ ኮሚቴዎችን ስምና የስልክ አድራሻ ማግኘት ከፈለጉ Academic ወይም Administration  በሚለው ገብተው በቀላሉ ያገኛሉ፡፡
 4. አስተያየት ወይም ጥቆማ እንድሁም ጥያቄዎትን በኢሜል ለመላክ ከፈለጉ Contact Us በሚለው ገብተው contact form በመጫን የሚሰጡትን አስተያየት ለት/ቤቱ ከፍተኛ ሃለፊዎች መላክ ይችላሉ፡፡ በ24 ሰዓት ውስጥም መልስ ያገኛሉ፡፡
 5. ዌብሳይቱን በፈለጉት የውጭ ቋንቋዎች መጠቀም ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በዉጭ የሚኖር ወይም የውጭ ቋንቋ ጀርመንኛ ወይም አረብኛ ብቻ የሚችል ወላጅ ብሎ በመግባት በቀኝ ጠርዝ ላይ ከሚታየው ሳጥን ውስጥ ቋንቋ/ Language በመምረጥ በቀላሉ መገልገል ይችላል፡፡
 6.  ዌብ ሳይቱ ሁሉንም የት/ቤቱን ባለድርሻ አካላት የሚያሳትፍ ነው፡፡ ተማሪዎች ፤ ክበባት እንድሁም መምህራን ሥራዎቻቸውን ለሌሎች ማካፈል ይችላሉ፡፡
 7. በዌብ ሳይቱ የግራ ረድፍ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ Online Resources የሚለውን በመክፈት የተለያዩ ትምህርት ነክ መልመጃዎች የሏቸው ሌሎች ዌብሳይቶችን በመክፈት ተማሪዎች መጠቀም ይችላሉ፡፡
 8. ወላጆች ወይም ተማሪዎች የዓመቱን የትምህርት ካሌንደር ለማወቅ ፤ የፈተናዎችን ፕሮግራም ለማወቅ Academic Calendar በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

 • በተማሪዎች መታወቂያ ደብተር ላይ የተገለጸው የተማሪ መታወቂያ ቁጥር ለሁልጊዜ ማስታወስ ወይም ጽፎ መያዝ ያስፈልጋል
 • በተማሪ መታወቂያ ደብተር ላይ በስህተት የተጻፈው የዌብሳይታችን አድራሻ ስህተት ስለሆነ ተብሎ እንዲስተካከል እንጠይቃለን፡፡

መልካም ጊዜ

ጳውሎስ ገመቹ

ፕሪንሲፓል

First Cycle Director Message

ለመኮ ቢሊ ት/ቤት ተማሪዎች፤መምህራንና ወላጆች እንኳን ለ2009 የት/ት ዘመን አደረሳችሁ እያልኩ የ2009 ት/ት ከጀመርን እነሆ 2ኛ ወራችንን ጨርሰናል፡፡ በእነዚህም 2 ወራት ውስጥ የመማር ማሰተማሩ ሥራ በተሳካ ሁኔታና በእቅዳችን መሠረት ተከናውነዋል፡፡

 

     የ1ኛ ሴሚሰተር የመጀመሪያ ፈተና /ቴስት/ለተማሪዎቻችን የሰጠን ሲሆን በህዳር 12 እና 13/09 ዓ.ም ደግሞ 2ኛ ቴስት ለ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች /ከኬጂ-6ኛ/ክፍል ይሰጣል፡፡

 

     በመሆኑም ተማሪዎች እንዲትዘጋጁ ወላጆች ተማሪዎቻችንን እንድታበረታቱና ጥሩ ውጤት እንዲያሰመዘግቡ እንዲታደርጉ መምህራንም የልፋታችሁ  ፍሬ ያማረ እንዲሆን ተማሪዎቻችሁን በበለጠ እንደታበቁ አሳሰበለሁ፡፡

 

  አብዲ ዮናስ የ1ኛ ደረጃ ር/መምህር

 

 

PRIMAY SCHOOL HOMEROOM TEACHERS

 

No

HOME ROOM TEACHER

GRADE

TELEPHONE No

1. 

BIKILTU TADESSE

1A

0967-47-23-38

2. 

EYERUSALEM YESFALEM

1B

0910-37-73-30

3. 

ALEMAYEHU BEKELE

1C

09

4.

MEMBERE TSEGAYE

2A

0910-76-19-50

5.

FIKERTE YILMA

2B

0925-32-36-30

6.

GIRMA TIBEBU

2C

0912-21-77-43

7. 

YOHANNES GETAHUN

3A

0911-96-23-26

8. 

NATSANET MUSIE

3B

0940-23-62-60

9. 

ABEL TADESE

4A

0912-22-15-94

10.

MUNAYE IDEA MEGERSA

4B

0912-82-05-95

11. 

ENGDAWORK GEBRU

4C

0912-30-34-93

12. 

SINAN NEGASH

5A

0926-66-13-75

13. 

ABDULEKADIR AKEEL

5B

0910-73-19-84

14 .

KANGEW GETACHEW

6A

0911-86-36-00

15.

TADELU FIKADU

6B

0921-17-33-00

16.

ESTIFANOS TILAHUN

7A

0911-02-73-85

17.

ASRAT SHIFERAW

7B

0934-85-28-08